ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት በያመቱ 300 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ።
ተቋሙ በሃገራችን የ8 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ዕቅድ ይዟል። የሳፋሪኮም ዋና ኃላፊ ፔተር ኔግዋ እንዳሉት ኢንቨስትመንቱ ለባለሙያዎች ገበያው የሚፈልገውን መሰረተ ልማት ለማሟላት ይረዳቸዋል ብለዋል።
እስካሁንም የ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማድረጉ ይታወቃል። ተቋሙ የኢንቨስትመንት መጠኑን ማሳደጉ በመላ ሀገሪቱ ያለውን የኔትወርክ ትስስር ለማስፋት ያለመ ነው ብሏል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-24
