ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ትልቁ ተራራ ሰደድ እሳት ገጠመው ተባለ

የታንዛንያ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት እየታገሉ ነው ተባለ።

ስለጉዳዩ የአካባቢው ባለስልጣናት የገለጹ ሲሆን ከ300 በላይ ሰዎች በአፍሪካ ትልቁ ተራራ ላይ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት በመረባረብ ላይ ናቸው ብለዋል።

ሰደድ እሳቱ በካራንጋ ካምፕ አቅራቢያ በተራራው የ4 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ በደቡባዊ ክፍሉ እንደተከሰተ ተገልጿል።

እሳቱ በምን ምክንያት እንደተነሳ ባለስልጣናቱ ያሉት ነገር ባይኖርም ተራራው መሰል አደጋን ካስተናገደ ከሁለት ዓመታት በኋላ ያሁኑን እንዳስስተናገደ ተጠቁሟል።

በሰሜናዊ ምስራቅ ታንዛንያ የሚገኘው የኪሊ ማንጃሮ ተራራ የ5 ሺህ 895 ሜትር ከፍታ አለው።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-24