በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ስድስት ወራት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ59 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 84 የትራፊክ አደጋዎች መከሰቱን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ ተናግረዋል፡፡ በደረሰው አደጋ በ59 ሰዎች ላይ ሞት ፤በ26 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ29 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ ከ435 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ በ2014 የደረሰው የትራፊክ አደጋ ካለፈው ዓመት 2013 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ58 አደጋዎች መቀነሱ ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም በስድስት ወራት ውስጥ 225 ሺሕ 715 አሽከርካዎች ላይ ቁጥጥር ተደርጓ ፡፡ 21 ሺሕ 931 አሽከርካሪዎች ህግ እና ደንብን ጥሰው በመቀጣታቸው 7 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ገቢ መደረጉን ሰምተናል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2022-01-11
