ሀገሬ ቲቪ

የተመድ መርማሪ ቡድን ወደ ዩክሬን ሊያቀና ነው

የተባበሩት መንግስታት የኒኩሌር ተቆጣጣሪ ኤጅንሲ መርማሪ ቡድኑን ወደ ዩክሬን ዳግም ሊልክ ነውኤጅንሲው ይህን የወስነው ሩሲያ ዩክሬን ላይ ያቀረበችውን ክስ ለማጣራት ነው።

የሩሲያ ክስ ዩክሬን የሬዲዮ አክቲቭ ጨረር እና ዩራኒየምን የያዝ ጅምላ ጨራሽ ቦንብ ለመጠቀም አቅዳለች የሚል ነው።

የዩክሬን ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ዘለንስኪ ግን ሩሲያ ራሷ ለመተቀም ያቀደችውን ነው በእኛ የምታሳብበው በሚል ክሱን አጣትለውታል።

ሁለቱ የሚካሰሱበት ይህ ቦንብ ደርቲ ቦንብ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን ጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለ ነው።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-25