የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን እንዳይገቡ መከልከል ዘላቂ መፍትሄ እንደማይሆን ተገለጸ።
መንግስት በቅርቡ 39 የሚሆኑ ምርቶችን ለማስገባት ዶላር እንደማይፈቅድ ማስታወቁ ይታወሳል። ይህንን አስመልክቶ ማብራርያ የስጡን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ዳካቲ ዓለሙ ምርቶች እንዳይገቡ መከላከላችን በውጭ ምንዛሬ በኩል የገጠመንን እጥረት አሳሳቢ ለመሆኑ ማሳያይሆን ይሆናል እንጂ ዘላቂ መፍትሔ አይደለም ብለውናል።
ዶ/ር ዳካቲ የህገ ወጥ ምንዛሬው ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ፈተና መሆን ላይ መድረሱ ሀገሪቱን የመጉዳት ፍላጎት ያላቸው አካላት በህገወጥ ተግባሩ በሰፊው ተሳታፊ እየሆኑ ስለመምጣታቸው መገመት አያዳግትም ብለዋል።
የውጭ ምንዛሬ አቅምን በዘላቂነት ለማሳደግ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት ብሎም የኤክስፖርት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-25
