ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ

16ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሔድ ጀምሯል።የጋራ ስብሰባው በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚወያይ ተጠቁሟል።

በመድረኩ ሙያተኞች የሁለቱን ሀገራት የምጣኔ ሀብትና ሌሎች ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከርና መሰናክሎችን ማስወገድ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተው መፍትሔ ያመላክታሉ ተብሎ ይተበቃል።

በምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ እንዲሁም በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መስኮች ትብብርን ማጠናከርና ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከር በስብሰባው ለውይይት የተያዙ አጀንዳዎች ናቸው።

ስብሰባው ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት ይካሄዳል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-25