መንግስት ግልጸኝነት የጎደለውን አሰራር ለማስቀረት እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አስተዋፅኦ ለማድረግ በመንግስት በኩል የሚደረጉ ማንኛውም ግዢና ጨረታዎች ኤሌክትሮኒክ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን በንግዱ ዘርፍ ከተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የ ኤሌክትሮኒክ ግዢን በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
በወረቀትና በሰው ንክኪ ይተገበሩ የነበሩ ስራዎች ኢ ፍትሀዊ ፤ ግልጸኝነት የጎደላቸው እንዲሁም ፤ ጊዜና ወጪ አባካኝ በመሆናቸው ይህን መተግበሪያ ለማበልጸግ እንዳስገደዳቸው የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ሁሉም የንግዱ ማህበረሰብ እስከ ህዳር ሰላሳ ቀን በዚህ ሲስተም ተመዝግቦ ወደ ስራ መግባት አለበት ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች በበኩላቸው የቀደሙ ስራዎች ከወረቀትና ከሰው ንክኪ ነፃ አለመሆናቸው ለስራችን እንቅፋት ነበር ብለዋል።
አሠራሩ ከገቢዎች ፣ ከመንግሥትና የግል ባንኮች፣ የመድን ተቋማት እንዲሁም ከቴሌ ብር አገልግሎት ጋር የተሣሠረ ሲሆን ተጫራቾች በመሀል ከሚገቡ ደላላዎች ነጻ በመሆን ካሉበት ሆነው በበይነመረብ አማካኝነት በየትኛውም የመንግስት ጨረታዎች ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-25
